የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች እስርና የኢሰመኮ መግለጫ

Your browser doesn’t support HTML5

የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች እስርና የኢሰመኮ መግለጫ

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ከህወሃትና “ሸኔ” ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 208 ሰዎች መያዙን ገልጿል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በተደረገ ፍተሻም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች እንደተገኙ አስታውቋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ሽብርተኝነትን በመደገፍ ተጠርጥረው የሚያዙ ዜጎች ብሔር ተኮር የመሰለ የአያያዝ ችግርም የሚታይበት ነው ሲል ስጋቱን ገልጿል።

በድሬዳዋ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ለጥርጣሬ በሚያበቃ መነሻ እንጂ በማንነታቸው አይደለም ያለው ፖሊስ “የአያያዝ ችግርም የለም ነው” ብሏል።