የአሜሪካ አምባሳደር ስለአጎአ ተጠቃሚ ሴቶች

Your browser doesn’t support HTML5

የአሜሪካ አምባሳደር ስለአጎአ ተጠቃሚ ሴቶች

በምጣኔ ኃብት ልማት ያልተራመዱ የአፍሪካ ሃገሮች ከታሪፍ ነፃ በሆነ ንግድ ከገበያዋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዩናይትድ ስቴትስ የከፈተችው አጎአ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ዕድል ሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሴቶችን ህይወት እየደገፈ መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ዛሬ ተናግረዋል።

አምባሳደር ፓሲ የኢንዱስትሪ ፓርኩንና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲን ዛሬ ከጎበኙ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት እንዲጠናከር አገራቸው ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል።