ሁለቱ የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

አሐዱ ሬዲዮና ቴሌቭዥን

አሐዱ ሬዲዮና ቴሌቭዥን

ከሽብርተኛ ድርጅት ተልዕኮ በመቀበል እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተዋል በሚል ጥርጣሬ ፖሊስ ሁለት የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ወንጀል ጠርጥሪያታለሁ በሚል ፖሊስ ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ያዋላት የአሐዱ ራዲዮ 94.3 ጋዜጠኛ ሉዋም አታክልቲ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ስትቀርብ፣ በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠረው በጣቢያው የዜና ክፍል ኃላፊ የሆነው ክብሮም ወርቁ ደግሞ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ ዙሪያ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ፈቅዷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ሁለቱ የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው