በቦረና ዞን በበልግ እና ክረምት ዝናብ በመጥፋቱ የቀንድ ከብቶች እየሞቱ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በቦረና ዞን በበልግ እና ክረምት ዝናብ በመጥፋቱ የቀንድ ከብቶች እየሞቱ ነው

በቦረና ዞን በበልግ እና ክረምት ዝናብ በመጥፋቱ ከአራት ሺህ በላይ ከብቶች መሞታቸዉ ተነገረ።

በደቡብ ኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በጊዜዉ መዝነብ የነበረበት ዝናብ በመዘግየቱ በላይ የቀንድ ከብቶ መሞታቸውን የዞኑ ነዋሪዎች ገልጹ።

ነዋሪዎቹ ይህ ክስተት መታየት ከጀመረ አንድ ወር መሆኑን ተናግረው፣ በዚህም በሺሕዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች እንደሞቱ ነው የገለጹት።

የቦረና ዞን የእንስሳት ሀብት ቢሮ በበኩሉ በእስካሁን ከአራት ሺሕ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን፣ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ኤጀንሲ በዚህ ሳምንት እርዳታ እንደሚያደርስ ገልጿል።