የጆንሰን ኤንድ ጆንሰኑን የኮቪድ ክትባት

  • ቪኦኤ ዜና

ዩናይትድ ስቴትሷ ሰሜን ምዕራባዊ ዋሽንግተን ክፍለ ሃገር ውስጥ በአንድ ጊዜ የሚሰጠውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰኑን የኮቪድ ክትባት የተከተበች ሴት እጅግ የተወሰኑ በብዛት በማያጋጥም ከደም መርጋት ጋር የተያያዘ ችግር ምክንያት ህይወቷ ማለፉ ተገለጠ።

ስሟ ያልተለገለጸው በሰላሳዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የነበረች ሴት ክትባቱን ከወሰደች ከሁለት ሳምንት በኋላ ትሮምቦሲስ ዊዝ ትሮምቦሳይቶፒኒያ በሚባል የደም መቋጠር ህይወቷ ማለፉን ነው የክፍለ ሀገሯ የጤና ባለሥልጣናት የገለጹት። የደም መቋጠር ለህልፈት ያደረሳት አራተኛ ሴት እንደሆነች ተመልክቷል።

ባለፈው ሚያዝያ የህን ክትባት በወሰዱ ከሃምሳ አመት በታች በሆኑ በርከት ያሉ ሴቶች ላይ ያልተለመደ የደም መቋጠር መከሰቱ መግለጹን ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ሲዲሲ እና የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ኤፍዲኤ የጆንሰኑን ክትባቱን መስጠት ለአጭር ጊዜ አስቁመው፣ በኋላ እገዳውን አንስተዋል።

ሆኖም ኩባኒያው ክትባቱ የደም መርጋት አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እንዳይለየው ታዟል። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ቁጥሩ ወደአስራ አምስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሰው የጆንሰን ኤንደ ጆንሰኑን ክትባት ተከትቧል።