ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎት አዲስ መተግበሪያ ተዘረጋ

Your browser doesn’t support HTML5

ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎት አዲስ መተግበሪያ ተዘረጋ

ባለፈው ሀምሌ መንግሥት በመላው ዓለም ከሚገኙት ኤምባሲዎችና ቆንስላዎቹ ውስጥ ከፊሎቹን ለመዝጋት ማሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ምክንያት የቀረበው ዋነኛው ምክንያት አላግባብ ይወጣል የተባለው ወጭ ነው፡፡

አብዛኞቹን የዲሎማቲክ ሥራዎች ከአዲስ አበባ ሆኖ መስራት እንደሚቻል የገለጹ ሲሆን፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያን የአገልግሎት ጥያቄዎች የሚያሟላበት መንገድም አብሮ ማዘጋጀቱንም ደግሞ የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ የዲጂታል መተግበሪያ እስከ 100 ሺ ሰዎችን ማስተናገድ እንችላለን ይላሉ፡፡ ይህ ወጭ በቀመነስና በምጣኔ ሀብቱ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ምን ይሆናል?