“ህወሓት ኤርትራን በማጥቃት ለጦርነት እየገፋፋ ነው” የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

Your browser doesn’t support HTML5

"ህወሓት ኤርትራን በማጥቃት ለጦርነት እየገፋፋ ነው" የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

“ህወሓት ኤርትራን በማጥቃት ለጦርነት እየገፋፋ ነው” ሲሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ከስሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 76ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በቪዲዮ ቀድሞ በተቀረፀ መልዕክት ትናንት ባደረጉት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮፓ አጋሮቿ “የህወሃትን አደገኛ አካሄድ ለመደገፍ እያደረጉ ነው” ያሉትን ጥረት ኮንነዋል።

“በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ችግር ሊፈታ የሚችለው በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ ቀናነት የተሞላበት ድርድር ብቻ ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል የኒው ዮርክና የአካባቢዋ ስቴቶች ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ጠቅላላ ጉባዔው እየተካሄደ በነበረበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ትናንት ሰልፍ ወጥተዋል።