ታሊባኖች “ወንጀል የሚፈጽሙ በሽሪያ ህግ ይቀጣሉ” አሉ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ምዕራብ አፍጋኒስታን ሄራት ከተማ

በምዕራብ አፍጋኒስታን ሄራት ክፍለ ግዛት የሚገኙ የታሊባን ባለሥልጣናት ትናንት ሰኞ ባወጡት መግለጫ ወንጀል ፈጽመው የተገኙ ወንጀለኞች በሸሪያ ህግ መሠረት እንደሚቀጡ ይፋ አድርገዋል፡፡

የታሊባኑ መግለጫ የመጣው የጠለፋ ክስ የተመሰረተባቸው አራት የታሊባን ተዋጊዎችን ባላፈው ቅዳሜ ህዝብ በሚሰብበብት የከተማ አደባባይ ላይ ሰዎችን በስቅላት ከቀጡ በኋላ ነው፡፡