በአፍጋኒስታን ካቡል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ 13 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሃይሎች እና ከ90 በላይ አፍጋንስታናዊያን ሰዎች በላይ ሕይወታቸውን ሲያጡ በቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው የአሜሪካ ወታደሮችም ለሕክምና ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ በዛሬው ዕለት በረራዎች እንደገና በመጀመራቸው አፍጋኒስታንን ለቀው ለመውጣት በዚያው ስፍራ በርካታ ሰዎች ተሰባስበዋል፡፡
ይሁን እንጂ የዎልስ ትሪት ጆርናል እንደዘገበው ደግሞ ሌላ ፍንዳታ ሊከሰት ይችላል የሚል ነገር በመሰማቱ ብዙ ሰዎች ዛሬ አርብ አካባቢውን ለቀው መሄዳቸው ታውቋል፡
በሌላ በኩልም የዩናይትድ ስቴት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ባሰሙት ንግግር “ይሄንን ጥቃት ለፈጸማችሁ እና አሜሪካንን ለመጉዳት ምኞት ያላችሁ ሰዎች፣ ይህንን ተረዱት ይቅር አንላችሁም!” ሲሉ አጥቂዎቹን ዋጋ እንደሚያስከፍሏቸው ቃል ገብተዋል፡፡
ይህን ተክትሎም በዋይትኋውስ የዩናይትድ ስትቴስ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ተውለብልቧል፡
Your browser doesn’t support HTML5