የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ቃለ ምልልስ አልሰጡም

ለማ መገርሳ

ከትላንት በስቲያ ሐምሌ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ በአሜሪካ ድምፅ ኦሮመኛ ቋንቋ ላይ ቀርበው መናገራቸውና እና ቀደም ሲል በማኅበራዊ መገናኛ ላይ እርሳቸው እንዳሉበት ተጠቅሶ የተሰራጨን ሌላ ወሬ መነሻ አድርገው ስማቸው ያለ አግባብ እየተነሳ መሆኑን ጠቅሰው ማስተባበያ መስጠታቸው በፌስ ቡክ እና በትዊተር ከፎቶግራፋቸው ጋር ተዳብሎ በመሰራጨት ላይ ይገኛል።

አቶ ለማ መገርሳ ቃለ ምልልስ እንደሰጡ ተደርጎ የተሰራጨው ወሬ በስም እና በምስል የሚያወቁና በይፋ በሚጠቀሟቸው ገፆች ላይ ጭምር የተሰራጨ ሲሆን ፣ በተጨማሪም አድማጮቻችን በስልክ እና በኢሜል ትክለኛውን መረጃ እንድንሰጣቸው ጠይቀውናል። ሆኖም አቶ ለማ መገርሳ ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ምንም ዓይነት ቃለ ምልልስ አልሰጡም።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ድምፅ የኦሮመኛ ቋንቋ ዋና አዘጋጅ ነሞ ዳንዲ “በቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት በኩል እንኳንስ አቶ ለማን አግኝቶ ቃለ ምልልስ ማድረግ ይቅርና ሐሳቡም አልቀረበም የተደረገም ሙከራ የለም’ ያለ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የቋንቋዎች ዘገባ አቀራረብን ጨምሮ ተጨማሪ ምላሽ ሰጥቷል።

የተዛቡ መረጃዎች፣ የጥላቻ ንግግሮችና የሐሰት ዜናዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ተፅኖን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ድምፅ ጋቢና ቪኦኤ በተሰኘው የጋቢና ማጣሪያ ፕሮግራም ላይ በስፋት ስናቀርብ የቆየን ሲሆን ከሚቀትለው ሳምንት ጀምሮ በመደበኛው የሦስት ሰዓት ፕሮግራማችን የቪኦኤ - ማጣሪያ በተሰኘ ፕሮግራማችን በአዲስ ፕሮግራም ዝግጅቱን ይዘን እንጠብቃችኋለን።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ቃለ ምልልስ አልሰጡም