“በአማራ ክልል ውስጥ ማንኛውም የመንግሥትና የግል መሳሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ከነገ ጀምሮ ይክተት” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ዛሬ እሁድ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጡት መግለጫ ጥሪ አቀረቡ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት በዚህ መግለጫ አሸባሪ ሲሉ የጠሩት ህወሃት “በተለያዩ ግንባሮች ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ የማጥቃት ሙከራእያደረገ ነው” ያሉ ሲሆን ሕፃናት እና አዛውንት በውጊያው ላይ በማሰለፍ ላይ ይገኛል ብለዋል። “የሕወሃት ዓላማም የአማራን ሕዝብለማጥቃትና ኢትዮጵያና ለማጥፋት ነው” ብለዋል።
በሌላ በኩል የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጥሪ ከማድረጉ አስቀድሞ ከትላንት በስቲያ መግለጫ የሰጡት የአፋር ክልል ፕሬዚዳንትአወል አልባ በአፋር ሕዝብ ላይ ጥቃት ፈፅሟል ያሉትን ከአዋሳኝ ትግራይ ክልል የገቡ አማፂ ተዋጊዎችን ሕዝቡ እንዲወጋ ጥሪአስተላልፈዋል።
(ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5
የዛሬውን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድ መግለጫ በዘገባው ያስነበበው ሮይተርስ የዜና ወኪል በጉዳዩ ላይ ከህወሃት ቃል አቀባይ አቶጌታቸው ረዳ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ገልጿል።