ባህርዳር —
የአማራ ክልል መንግሥት ወደ ትግራይ የሚጓጓዙ የሰብዓዊ የእርዳታ እህሎችን በጥብቅ በመፈተሽ በፍጥነት ለሕዝቡ እንዲደርስ የማድረግ ሥራ እየሠራ መሆኑን ገለፀ። የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባደረጉት ቆይታ “የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች የሚፈተሹት ለደህንነት ነው” ብለዋል ከሰሞኑ ህወሃት የአማራ ልዩ ኃይል ከወልቃይትና ራያ ይውጣ ሲል ስላወጣው መግለጫ ተጠይቀው የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ለአማራ ሕዝብ ዶሴው የተዘጋና ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5