“ወልቃይት፣ ጠገዴንና ራያን በድጋሚ፣ በጉልበት ለመውሰድ የሚደረግ እንቅስቃሴ፤ በአማራ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም” ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል::
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ከምዕራብ ትግራይ ይውጣ የሚለውን የሕወሃት ቅድመ ሁኔታ ተከትሎ ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት መግለጫትንኮሳ የሚፈጽም ካለ ክልሉ ተዘጋጅቶ እንደሚጠብቅ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፤የኤርትራና የአማራ ኃይሎች፤ ከትግራይ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ማሳሰባቸው ተገልጿል::
(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይ ያዳምጡ።)
Your browser doesn’t support HTML5
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መግለጫ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድን አነጋግረዋቸዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በትግራይ ግጭት ያሉበትወገኖች በሙሉ በአስቸኳይ ድርድር አድርገው ዘለቄታ ያለው ተኩስ አቁም ያደርጉ ዘንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን በአጽንዖትአሳስበዋል።
ወደ ትግራይ ክልል የሚያስገቡ ድልድልዮች መፍረሳቸውን እና ሌሎችም የክልሉን ተደራሽነት የሚያሰናክሉ አድራጎቶችን የውጭ ጉዳይሚንስትር ብሊንከን ማውገዛቸውን ቃል አቀባዩ እክለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈው ዐርብ ባካሄደው ስብሰባ የዘረዘራቸውንርምጃዎች ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እንዲያረጋግጡ የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያሳሰቧቸው መሆኑን ቃል አቀባያቸውኔድ ፕራይስ ገልጸዋል።
በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የተጠየቁት ርምጃዎች የኤርትራ እና የአማራ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ፥ ትግራይውስጥ ለተቸገሩት ማኅበረሰቦች ሰብዐዊ ርዳታ በተሟላ፥ ባልተደናቀፈ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ተደራሽ እንዲደረግ፥ የሰብዓዊመብት ጥሰት እና የጭካኔ አድራጎት የፈጸሙ ተጠያቂ የሚሆኑበት ግልጽ ሂደት እንዲጀመር ፥ የኢትዮጵያ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥድንበሮች በኃይል ወይም ሕገ መንግሥቱን በጣሰ መንገድ የማይቀየሩ መሆኑ እንዲረጋገጥ የሚሉትን እንደሚያካትት መግለጫውዘርዝሯል።
ከዚህም በተጨማሪ የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድን ባነጋገሩበት ወቅትበሀገሪቱ ላሉት ጎሳን መሰረት ያደረጉ እና ፖለቲካዊ ክፍፍሎች ዘለቄታ ያለው መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችል ፈታኝ ሥራ ለመጀመር ይቻልዘንድ አሳታፊ የፖለቲካ ንግግር መክፈት በአጣዳፊነት የሚያስፈልግ መሆኑን አጥብቀው ማሳሰባቸውን መግለጫው ጨምሮ ገልጿል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ፍላጎት ላላቸው አካላት የበረራ ፈቃድ መስጠቷ ተዘገብቧል። መጀመሪያላይ በአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ተቋም የማህበራዊ መገናኛ ገጾች ቀጥሎም በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን እንደተሰማው ፈቃዱመሰጠት የተጀመረው ከትናንት በስትያ ሰኞ ዕለት ጀምሮ ነው።
ይህ በእንዲህ እያለ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ላይ ግድያ ሳይፈጸም እንዳልቀረ የሚነጋሩ ሪፖርቶች እንደደረሱትየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ አስታወቋል።
ባለፈው ሳምንት ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ በተመለከተ የቀረቡ መረጃዎችን በከባድ ትኩረት በመመልከት በፍጥነት ሰራተኞቹን፣አጋሮቹን እና በሽሬ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን እንዳነጋገረ ይፋ አድርጓል ። እስካሁን ግን ያገኘናቸውን መረጃዎች ለማረጋገጥአልቻልንም ብሏል ተቋሙ። ከትግራይ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት እየጣርን ቢሆንም በስልክና ኢንተርኔት ግንኙነት ችግር ምክንያትጥረታችን እስካሁን አልተሳካም፤ እንደተሳካ የምናገኘውን ይዘን እንመለሳለን።