በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች የተወሰኑት በእግራቸው እየወጡ ነው

የአዲግራት ከተማ ከላይ ሲታይ

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች፣ በእግራቸው አካባቢውን እየለቀቁ፤ ወደ ወሎና አፋር አካባቢዎችመግባታቸው እየተነገረ ነው፡፡ መቀሌ በሚገኘው ሃይደር ሆስፒታል የተግባር ትምህርት ላይ የነበሩና ዘንድሮ የምርቃን ሥነ ስርአታቸውንሲጠባባቁ የነበሩ የሕክምና ተማሪዎችን ጨምሮ ከሰላሳ በላይ ተማሪዎች እንደ አመችነቱ በተሸከርካሪና በእግራቸው አቆራርጠው ደሴከተማ መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ትምርታቸውን በተረጋጋ መንፈስ ለማስቀጠል የሚያስችል የስነ ልቦና ዝግጅትና ምቹ ሁኔታ ስሌለለ የትምሕርት ገበታቸውን ለቀውአቆራርጠው መውጣታቸውን ተናግረዋል

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ከቀናት በፊት በይፋዊ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት ተማሪዎቹ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙናየሁለተኛ መንፈቅ ኣመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ናቸው ማለቱ ይታወቃል፡፡

ሁለት ልጆቼ ተመልሰውልኛል የሚሉት ታጠቅ አበበ የተባሉ ወላጅ በዚህ ሁኔታ ተማሪዎቹን ትመህርት እንዲከታተሉም ሆነ ፈተናእንዲወስዱ ማድረግ ተገቢ አይደለም ባይ ናቸው፡፡

በትምህርት ቤት ግቢዎቻቸው ውስጥ የመንግሥት ደጋፊና ተቃዋሚ የሚል ፍረጃ በመፈጠሩ በተማሪው መካከል ውጥረት መኖሩአካባቢውን ለቃ ለመምጣት እንዳስገደዳት የምትናገረው ደግሞ ሌላዋ የህክምና ተማሪ ሜላት በየነ ነች፡፡

ከትምህርት ግቢያችን ውጭ ያለው የትግራይ ህዝብ ላደረገልን ድጋፍና ተቆርቋሪነት ምስጋናችንን እንገልጻለን ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት አካባበዊውን መልቀቅ ተከትሎ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩተማሪዎች በእግራቸው መውጣት መጀመራቸው እየተሰማ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ከትግራይ ወደ አፋር ሰመራ የዘለቁ ተማሪዎችመኖራቸውን የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አረጋግጧል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር አመራርን ምላሽ ለማግኘት ብንሞክርም ሁሉም መገናኛ ብዙሐን በተገኙበት በቅረርቡየደረሱበትን እንደሚያሳውቁ ጠቁመው በተናጠል ግን ምላሽ እንደማይሰጡ ተገልጾልናል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ወላጆች ልጆቻቸው በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ተረድተው በመንግሥት የተጀመሩጥረቶችን እንዲደግፉ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች የተወሰኑት በእግራቸው  እየወጡ ነው