አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሰሜን ትግራይ የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ የነበሩ የኤርትራ ስደተኞችን ወደ ደቡብ ትግራይ ና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እያዛወረ መሆኑን አስታውቋል።
የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በትግራይ ጦርነት በስደተኞች ላይ የደረሰውን ጉዳት አኀዝ መሥሪያ ቤታቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞች ግን በተለይ ከትግራዩ ክስተት ወዲህ ያላቸው ስጋት መጨመሩን ተናግረው “ይደረግላቸው የነበረው ድጋፍም ቀንሷል” ብለዋል።
በሌላ በኩል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር /ዩ ኤን ኤች ሲ አር/ በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2020 ዓ.ም. ከ82.4 ሚሊዮን በላይ ሰው በግጭቶች ምክንያት ከቤት ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5