የኢትዮጵያ ምርጫ የመጨረሻ ዝግጅቶች

  • እስክንድር ፍሬው

ሶሊያና ሽመልስ

ልክ የዛሬ ሳምንት ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ከዚህ ምሽት ጀምሮ ወደተለያዩ አካባቢዎች እንደሚላኩ የጠቀሱት የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ዜጎች ድምፅ እንዲሰጡ የማበረታታት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

45 ሺህ የሚሆኑ የአገር ውስጥ ታዛቢዎችም ፈቃድ ወይም ባጅ መውሰዳቸውን አስረድተዋል።

በፀጥታ እና በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው የዛሬ ሳምንት በማይካሄድባቸው 59 የምርጫ ክልሎች ደግሞ ጷግሜ 1 ቀን እንደሚካሄድ የኮምዩኒኬሽን አማካሪዋ አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ምርጫ የመጨረሻ ዝግጅቶች