ሱዳን ውስጥ የተካሄደው ተቃውሞ

  • ቪኦኤ ዜና

የሱዳን መንግሥት የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ድጎማ መስጠቱን እንደሚያቆም ማስታወቁን ተከትሎ ትናንት በዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ጎማ በማቃጠል ተቃውሟቸውን ገለጹ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ጂብሪል ኢብራሂም ከትናንት በስተያ ማክሰኞ በሰጡት ቃል የቤንዚን እና ናፍጣ ዋጋውን ከውጭ ማስገቢያው ወጪ፤ ማጓጓዣው እና ቀረጡና ነጋዴው የሚጠይቀው ትርፍ ይወስነዋል ብለዋል።

በአዲሱ የዋጋ ተመን መስረት የቤንዚን ዋጋ በሊትር ሰላሳ አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ሳንቲም ይገዛ የነበረው፣ ወደ ሰባ ሳንቲም ከፍ ሲል የናፍጣ ዋጋ ደግሞ በሁለት ዕጥፍ እንደሚጨምር ታውቋል።

መንግሥቱ ለምግብ ማብሰያና የቤት ማሞቂያ ለሚውል ወጭ የሚሰጠውን ማስተካከያውን መስጠቱን እንደሚቀጥል ታውቋል።