በቀድሞ የቦዝኒያ ሰርቦች የጦር አዛዥ ላይ የተመድ ፍ/ቤት ውሳኔ ይሰጣል

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ራትኮ ምላዲች

በዘር ማጥፋት፣ በጦር ወንጀል እና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ወንጀል በመፈጸም እአአ በ2017 የጥፋተኝነት ብይን የተላለፈባቸው የቀድሞ የቦዝኒያ ሰርቦች የጦር አዛዥ ላቀረቡት ብይን የተመድ ፍርድ ቤት ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል።

የሰባ ስምንት ዓመቱ ራትኮ ምላዲች በ1990ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት በተካሄደው በቦዝኒያው ጦርነት ስሬብሬኒካ ከተማ ውስጥ ከስምንት ሺህ በላይ አዋቂና ታዳጊ ወንዶች አስፈጅተዋል። ሳራዬቮ ውስጥ በሲቪሎች ላይ የማሸበር እና ሌላም ህገ ወጥ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው የዕድሜ ልክ እስራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

እርሳቸው ግን ወንጀሉን አልፈጸምኩም በሚለው ቃላቸው ጸንተዋል ፤ ጠበቆቻቸውም የተፈረደባቸው በህግ አፈጻጸም እና ሃቁን በማጣራት ረገድ በተፈጸመ ስህተት ስለሆነ እና በተፈጸመ ተግባር ሌሎች ተጠያቂዎች ከወንጀሉ ነጻ መባል አለባቸው አለዚያም ጉዳያቸው እንደገና መታየት አለበት ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።