የኢትዮጵያ መንግሥት “የኤርትራ ወታደሮች መውጣት ጀምረዋል” አለ

  • እስክንድር ፍሬው

ቢል ለኔ ስዩም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ክፍል ኃላፊ እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከትግራይ ክልል ሁኔታ አንፃር ያሉ ግልጽ በርካታ እውነታዎችን ማየት ተስኖታል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታውቋል።

የጽ/ቤቱ የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም በአንዳንድ ወገኖች የሚታየው እውንታዎቹን የመዝለል አካሄድ ጠቃሚ ውጤት አይኖረውም ብለዋል።

የኤርትራ ወታደሮችን መውጣት አስመልክቶ የተጠየቁት ኃላፊዋ በተደረሰበት ስምምነት መሠረት እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግስት “የኤርትራ ወታደሮች መውጣት ጀምረዋል” አለ