የወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂምና የአቃቤ ህግ ውዝግብ

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም

የህወሃት ሥራ አስፈፃሚ እና የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በህወሓት አመራሮች ላይ ለመመስከር ከተስማሙ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው ሃሳባቸውን ቀይረው “አልመሰክርም” በማለታቸው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ሊመሰርትባቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፀ።

ወ/ሮ ኬሪያ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የገለጡት ጠበቃቸው አቶ ሃፍቶም ከሰተ በህወሓት አመራሮች ላይ ለመመስከር ሥምምነት አልነበራቸውም ፤ በድብቅ ተቀርፆአል በተባለ ቪዲዮ ስላስፈሯሯቸው ነው የዛሬን ቀን ሲጠብቁት የነበረው ብለዋል።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ይህንን ሃሳብ እንደማይቀበል ገልፆ፤ በቂ መረጃ እንዳለውና መቅረብ በሚገባው ወቅት እንደሚያቀረብ አሳውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂምና የአቃቤ ህግ ውዝግብ