ነቀምት ላይ "ሦስት" ፀሐይ ታየች

በነቀምቴ ከተማ ዛሬ ጠዋት ፀሐይ ሦስት ሆና ታይታለች።

በነቀምቴ ከተማ ዛሬ ጠዋት ፀሐይ ሦስት ሆና ታይታለች፤ ክስተቱ ትዕንግርት ሆኖብናል ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎቿ ይናገራሉ። የተባለውን ክስተት አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አጠር ያለ ትንታኔ የሰጡት የኢትዮጵያ ስፔንስ ሳይንስ ማኅበር ባለሞያ አቶ ክብረት አፅበሃ

"ይህ ክስተት ፀሐይ አድማስ አካባቢ ስትወጣና አየሩ ቀዝቃዛ ሲሆን ጠጣር የበረዶ መሰል ንጥረ ነገሮች የፀሐይ ብርሃንን መልሰው በሚያንፀባርቁበት ወቅት የሚከሰት ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

የፀሐይ ብርሃን ጉዳት ሊያመጣ ስለሚችል

"ሰዎች በባዶ አይናቸውም እንዲመለከቱት አይመከርም" ሲሉ ባለሞያው አክለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ነቀምት ላይ "ሦስት" ፀሐይ ታየች