ነጆ ውስጥ ባለፈው ሣምንት ስለተፈፀሙ ጥቃቶች

Be

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ባለፈው ሣምንት “ታጣቂዎች አደረሱት” በተባለ ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።

አስተዳዳሪው አቶ ተሊላ ተረፈ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል "ጥቃቱን የፈፀሙት የጉሙዝ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ /ቤህነን/ ታጣቂዎች ሲሆኑ ሌላ ተጨማሪ አንድ ሰው አቁስለው ንብረትም ዘርፈዋል" ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱለዚም መሀመድ በሁለቱም ክልሎች ወሰንና ሌሎችም ቦታዎች ታጣቂዎች ጥቃት በመፈፀም የብሄር ግጭት እንዲመስል ጥረት ያደርጋሉ" ብለዋል።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልም ሆነ በሌሎች ሥፍራዎች ጥቃት በመሰንዘር ላይ ያሉት ባለፈው ሣምንት ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ የደረሰው የታጣቂ ቡድን አባላት አይደሉም” ሲሉ ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ነጆ ውስጥ ባለፈው ሣምንት ስለተፈፀሙ ጥቃቶች