ሀዋሳ —
በደቡብ ክልል ለሚመሰረተው 11ኛ የደቡብ ምዕራብ ክልል መተዳደሪያ ረቂቅ ህገ መንግሥት መዘጋጀቱን የውሳኔ ህዝብ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ፀጋዬ ማሞ ለቪኦኤ አስታወቀ።
ክልሉ ከተመሰረተ ከአንድ በላይ ማዕከላት ሊኖረው እንደሚችልም የውሳኔ ህዝብ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የፕሮጀክት ፅ/ቤት የጋራ ምክክር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የክልሉ መመስረተ በራሱ የመጨረሻ ግብ ባይሆንም የአከባቢው ህዝቦች አጥተነው የነበረውን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ችግር እንደሚፈታ ጠቅሰዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5