አምቦ —
ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ግንቦት ወር ልታካሂደው ባቀደችው ምርጫ ለመምረጥ እንዲሁም ላለመምረጥ ያቀዱ የማኅበረሰብ ክፍል አባላት መኖራቸውን ከአምቦ ከተማ የተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውሮ ያነጋገረው ዘጋቢያችን አስተያየቶቹን ልኮልናል።
“ለመምረጥ ካርድ ወስደናል። ይበጀናል፣ ይሆናል ላልነው የፖለቲካ ድርጅት ድምጻችንን እንሰጣለን” ያሉ እንዳሉ ሁሉ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ እንዳልወሰዱ የገለጹም አሉ።
የማይመርጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ ደግሞ በአምቦም ሆነ እንደ ክልሉ ሌሎች አማራጭ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው አለመሳተፍ እና ሌሎች ምክንያቶችን ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5