ባህር ዳር —
“በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ በየቦታው እየተፈፀመ ነው” ያሉትን ግድያና ጥቃት የሚያወግዙና ፍትሕን የሚጠይቁ ሰልፎች በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ዛሬም ቀጥለዋል።
ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው በዚህ ተቃውሞ የንግድ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዝግ ሲሆኑ እንቅስቃሴን የመገደብ አድማም ተካሂዷል።
የአማራ ክልል መንግሥት ትናንት በሰጠው መግለጫ “የንግድ ተቋማትን መዝጋትና የእንቅስቃሴ ገደብ አድማ የሚያዋጣ የተቃውሞ ስልት አይደለም” ሲል አሳስቧል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5