አምቦ —
በኦሮምያ ክልል ምእራብ ወለጋ የ2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲከናወን ዝግጅት እየተደረገ ነው ሲሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ገለፁ።
የፀጥታ ችግር ያለባቸው ስፍራዎች ተለይተው በተጠናከረ ጥበቃ ሊደረግ የሚችልበት ሁኔታ ላይ እየሰራን ነው ብለዋል አስተዳዳሪው።
በሌላ በኩል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋስ
"ምርጫው መከናወን ስላለበት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የድርድሩ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው" ብለዋል።
የኢትዮዽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በፀጥታ ችግር ምክንያት ሁለቱን ዞኖች ጨምሮ ሌሎች የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸውና የምርጫ ጣቢያ ያልተከፈቱባቸውን የሀገሪቱ አከባቢዎች አስታውቆ ነበር።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5