የጤና አዋቂዎች ስለአዳዲሶቹ የኮሮናቫይረስ

  • ቪኦኤ ዜና

"በየጊዜው አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች በስኬት እየወጡ ቢሆንም ያ ወረርሽኙን ድል ልንመታው ነው ማለት አይደለም" ሲሉ ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ጥበቃ አዋቂዎች አስገነዘቡ።

የላንሴት የኮቪድ-19 ኮሚሽን ግብረ ሃይል አባላት ዘ ኮንቬርሴሽን በተባለው መጽሄት ላይ ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሁፋቸው ከፊተኛው ይበልጥ ተላላፊ የሆኑት የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓይነቶችን ለመቆጣጠር ዓለም በከፍተኛ ሩጫ ላይ እንደሆነች አመልክተዋል።

አያይዘውም እየተቀያየረ ያለው የቫይረሱ ዝርያ አሁን ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉትን ክትባቶች እንዳይሰሩ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቅሰው፣ ልውጦቹ ዝርያዎች ጨዋታውን ቀይረውታል ብለዋል።

የጤና ኤክስፐርቶቹ ግብረ ሃይል አያይዞ ሦስት አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ልውጥ ብሪታንያ እና ደቡብ አፍሪካ በማስከተልም ብራዚል ላይ የተከሰቱትን ጨምሮ ልውጦቹ የቫይረሱ ዓይነቶች ስጋት መደቀናቸውን አስገንዝቧል።

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ በጠበቀ ስልት ተቀርጾ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ አዋቂዎቹ አሳስበዋል። ይህም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና የቤቶችና መሰል ዝግ ቦታዎችን አየር እንዳይታፈን ማድረግ እና የክትባት ዘመቻውን መቀጠልን እንደሚጨምር አብራርተዋል።