በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መስፋፋት ለመከላከል የወጣው መመሪያ 

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስን መስፋፋት ለመከላከል ባለፈው መስከረም የወጣው መመሪያ ዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ጠቅላይ አቃቤ አስታውቋል ።

መመሪያው አስገዳጅ የሆኑ የጥንቃቄ እምጃዎች የተካተቱበት እንደሆነ ተገልጿል።

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ የእጅ ማፅጃዎችን መጠቀምና ሌሎችም የጥንቃቄ እርምጃዎች

“አስገዳጅ” ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል ናቸው።

ሰርግና ለቅሶን የመሳሰሉ ማኅበራዊ ክንውኖችም መከናወን ያለባቸው ከሃምሣ ባልበለጡ ታዳሚዎች እንዲሆን ተወስኗል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መስፋፋት ለመከላከል የወጣው መመሪያ