ሳራ ኦባማ በ99 ዓመታቸው አረፉ

  • ቪኦኤ ዜና
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሴት አያት ኬንያዊቱ ሳራ ኦባማ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሴት አያት ኬንያዊቱ ሳራ ኦባማ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሴት አያት ኬንያዊቱ ሳራ ኦባማ በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው አረፉ።

ሳራ ኦባማ በኬንያ ኪሱሙ ክፍለ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል ሲታከሙ ቆይተው በዛሬው እለት ማረፋቸውን ቤተሰባቸው አስታውቋል።

ኬንያውያን በፍቅር “ማማ ሳራ” ብለው የሚጠሩዋቸው አረጋዊቱ የቀድም የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት አያት አግብተው የፕሬዚዳንቱን አባት ባራክ ኦባማ ሲኒየርን አብረዋቸው አሳድገዋል።

ፕሬዚዳንት ኦባማ የአባታቸውን የእንጀራ እናት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቋቸው እአአ በ1988 ኬንያን በጎበኙበት ጊዜ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግንኙነታቸው ቀጥሎ እአአ በ2009 በፕሬዚዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተዋል።