ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ በፕሬዚደንት ጆን ማጉፉሊ ማረፍ ለታንዛኒያ ህዝብ ሃዘኗን ገለጸች። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የታንዛኒያ እና የአሜሪካ ህዝብ ግንኙነት እንዲሻሻል መስራታችንን እንቀጥላለን ብሏል።
በማስከተልም የታንዛኒያ ህዝብ ሰብዓዊ እና መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ በሚያካሂደው ትግል እና ኮቪድ-19ኝን ለመዋጋት በሚያካሂደው ጥረት ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል አስረድቷል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በማናናቃቸው እና በመጠራጠራቸው በሀገራቸው ላይ ብርቱ ዓለም አቀፍ ነቀፋ አስከትለው ማጉፉሊ በስድሳ አንድ ዓመታቸው ማረፋቸውን ያስታወቁት ምክትል ፕሬዚዳንታቸው ሳሚያ ሱሉሁ የህልፈታቸው ምክንያት የልብ ድካም ህመም መሆኑን ገልጸዋል።
ማጉፉሊ እአአ ካለፈው የካቲት ወር መጨረሻ ወዲህ ከህዝብ ዓይን ተሰውረው የቆዩ ቢሆንም ከፍተኛ የመንግሥታቸው ባለሥልጣናት “በጣም ታመዋል” የሚለውን ወሬ ሲያስተባብሉ ከርመዋል።
ባለፈው ዓመት የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ በሦስት ቀን ብሄራዊ ጸሎት ኮቪድን አስወግደነዋል ብለው እንደነበር ይታወሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5