ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያውያን የማንበብ ባህል ከግዜ ወደ ግዜ እየቀነሰ መምጣቱ ያሳሰባቸው በአሜሪካን ሀገር ሚኖሶታ ክፍለ ግዛት የሚኖሩ ወጣቶች የማንበብ ባህልን ለማሳደግና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውይይትን ለማዳበር የሚረዳ 'ሆራይዘን' የተሰኘ የመፅሃፍ ክለብ በማቋቋም በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች አማካኝነት አንባቢያንን እያሰባሰቡ ይገኛሉ። አለማንበብ የእውቀት አድማሳችንን አጥብቦ ሁለንተናዊ እድገት እንዳናገኝ ማነቆ ሆኖናል የሚሉት ወጣቶች የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መፅሃፍትን በማንበብና በማወያየት አንድ አመት አስቆጥረዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5