ዋሺንግተን ዲሲ —
"ይሄ ሁላችንም የምናደርገው ነገር ነው። ዝናብ መጣ ሲባል ጃንጥላ ይዘን እንሄዳለን። ኮፊያ አደርገን መጠለያ እንፈልጋለን። ቫይረሶቹም በሚያጋጥማቸው ነገር ራሳቸውን መቀየር የተለመደ ነገር ነው" ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል።
ሃኪምዎን ይጠይቁ ለምሽቱ ከፍ ያለ ተስፋ ያሳደሩት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች በተፈለገው ፍጥነት መሰራጨት እና ሰዎች በጊዜ መከተብ ያለመቻላቸው ያሳደረውን ሥጋት ይመለከታል። ይህ ሁኔታ በተጨማሪም ራሱን የለወጠ የቫይረስ ዝርያ እንዲስፋፋ ሊያደርግ የሚችለውን አስተዋፅዖም ይመረምራል።
ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ መምሕር እና የክሊኒካልና ፋርማሲ አስተዳደር ሳይንስ ትምሕርት ክፍሎች ምክትል ሊቀመንበርም ናቸው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5