የሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥቃት በሚፈፀምበት ግዜ፤ ጥቃቱ በራስ ላይ እንደተፈፀመ መቆጠር እንዳለበት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ኃላፊዎች ገለፁ። በጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን ከአድማጮች ለተነሱ ጥያቄው ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዲሬክተር አቶ ዳን ይርጋና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ አጥኚ አቶ ፍሰሃ ተክሌ የሰዎች ሰብዓዊ መብቶች በሚጣስበት ጊዜ ጉዳዩን በተለያየ ጠርዝ ውስጥ በማስገባት ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ሃገሪቷን ከአዙሪት ውስጥ እንዳትወጣ ያደርጋታል ብለዋል።
በትግራይ ክልል የሚገኘውን የሰብዓዊ ሁኔታ አያያዝ እና ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮ ላይ አተኩሮ በተዘጋጀው በዚህ ውይይት ፤ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዎቹ፤ የሰዎች ሰብዓዊ መብቶች መጣስ ማንኛውንም ሰው ሊያሳስበው ይገባል የሚል ሐሳብ አንፀባርቀዋል።
(ሙሉ ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5
በተጨማሪም
ለአስተያየት እና ለጥያቄዎቻችሁ ጻፉልን፤ ደውሉልን።
202-205-9942 - በመጠቀም በውስጥ መስመር 14 በተቀረፀው የድምፅ መመሪያ መሰረት መልዕክትካስቀመጣታችሁ ይደርሰናል።
202-251-3505 - ለዋትስአፕ ብቻ
horn@voanews.com - በኢሜል
@voaamharic - በፌስቡክ ይላኩልን
#VOAAMHARIC - የትዊተር ገፃችንን በመጠቀም
አስተያያችሁን አካፍሉን።