የጉምዝ ታጣቂዎች በአዊ ዞን ጥቃት ማድረሳቸውን አስተዳደሩ ገለፀ

Awi Zone

Awi Zone

በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጓንጓ ወረዳ መንግሥት “የጉምዝ ታጣቂዎች ናቸው” ያላቸው በአርሶ አደሮች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገልጿል።

ትናንት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጋር በሚዋሰነው የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን “ጓንጓ” ወረዳ ሞጣ ቀበሌ ውስጥ ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ማሳቸውን በመሰብሰብ ላይ በነበሩ በአርሶ አደር ላይ ቀስት በማስፈንጠር ጥቃት ለማድረስቢሞክሩም የአርሶ አደሩ ቤተሰቦች ሮጠው ማምለጣቸውን የወረዳ ፖሊሲ ፅ/ቤት ኃላፊ ም/ኮማንደር ደምመላሽ ብርሃኑ ገልፀዋል።

በሲቪሎች ላይ የደረሰ ጉዳይ አለመኖሩን፣ ነገር ግን አጥቂዎቹ የአካባቢውን ፀጥታ የሚያስከብሩ ሁለት የልዩ ኃይል አባላትንና አንድ የሚለሽያ አባል መግደላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የጉምዝ ታጣቂዎች በአዊ ዞን ጥቃት ማድረሳቸውን አተዳደሩ ገለፀ