“ኦነግ ሸኔ” የተባለው ታጣቂ ቡድን በአማራና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃትእየፈፀመብንነው ሲሉ ቅሬታ ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ ሄደው የነበሩ የምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳነዋሪ ተናግረዋል::
ባህርዳር —
“ከሕውሃት ውድቀት በኋላ በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ዘርንመሰረት ያደረገ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ባሉ የሕወሓት ርዝራዞች ነው” ያለው ደግሞ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ነው::
መንግስት ሕግ የማስከበር እርምጃ እንዲወስድም ንቅናቄው ጠይቋል:: የኦሮሚያ ክልል መንግሥትበበኩሉ ከሰሞኑ ጥቃት ጋር በተያያዘ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉና እጃቸው አለበት ተብለውየተጠረጠሩ ከ800 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
አሁን ባለው የአገሪቱ ሁኔታ ከሕወሓት አመራሮች ምላሽ ለማግኘት የማንችል መሆኑ ይታወቃል። ከዚህአመራሮቹ የአሜሪካ ድምፅን ጨምሮ በሚሰጧቸው መግለጫዎች በሀገሪቱ በየትኛውም ሥፍራዎችየሚፈጠሩ ግጭቶችን ያባብሳል፤ ታጣቂዎችንም ይደግፋል የሚለውን ማስተባበላቸው ይታወሳል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5