በግጭት ቀጠና ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ያገለገለች የህክምና ባለሙያ

በወልዲያ ሆስፒታል ለተለያዩ ቁስለኞች የህክምና አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው መቅድም ባዬ

በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግስቱ መሃከል የተከሰተውን ውጊያ ተከትሎ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው በርካታ ዜጎች ህክምና ለመስጠት የህክምና ባለሙያዎች ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድን በማቋቋምና ግጭቱ ወደተከሰተባቸው በመሄድ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል። ከነዚህ መሀል በጋንዲ ሆስፒታል የአንስቴዥያ ባለሙያ የሆነችውና ከሌሎች የህክምና አጋሮቿ ጋር በመሆን በወልዲያ ሆስፒታል ለተለያዩ ቁስለኞች የህክምና አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው መቅድም ባዬ አንዷ ናት።

Your browser doesn’t support HTML5

በግጭት ቀጠና ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ያገለገለች የህክምና ባለሙያ

በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግስቱ መሃከል የነበረው መካረር ጥቅምት 24 በይፋ ወደ ጦርነት ከተሸጋገረ በኃላ በጦርነቱ ጉዳት የሚደርስባቸውን ዜጎችን ለማከም የሚችሉ በጎ ፈቃደኞች እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ። አዲስ አበባ በሚገኘው ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የማደንዘዣ (አንስቴዥያ) ባለሙያ ለሆነችው መቅድም ባዬ ይህ ጥሪ በሙያዬ ምን ላድርግ የሚለውን ጥሪ የመለሰላት ነበርና ጥሪውን ተቀብላ ለመመዝገብ አላመነታችም።

መቅድም ይህ ከፍርሀቷ ብዙም አብሯት አልቆየም። ከሚያጋጥመኝ ይልቅ የምረዳው ነገር ይበልጥ ይሆናል የሚለው ስሜቷ አሸነፈና ከሌሎች 48 የጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን የመጀመሪያዎቹ በጎ ፈቃደኛ በመሆን ወደ ወልድያና ቆቦ የሚገኙ ሆስፒታሎች አቀኑ። መቅድምም በህይወቴ አይቼው የማላውቀውን የሀገር መስዋትነት ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁ ትላለች።

መቅድም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በጦርነቱ ቆስለው የሚመጡት ዜጎች ለሀገራቸው ያለው ፍቅር ልብ የሚነካ ቢሆንም ጦርነት ግን አስከፊ መሆኑንም አይቻለሁ ትላለች።

በትግራይ ክልል ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ ከአዲስ አበባ በበጎ ፈቃደኝነት ወደ ቦታው ካቀኑት የህክምና ቡድን አባላት መሀል ነርሶች፣ የቀዶ ጥገና ሀኪሞች፣ የአጥንት ስፔሻሊስቶችና ሌሎች የህክምና አመራሮች ይገኙበታል። መቅድም ከዚህ ቡድን ጋር በወልድያና በቆቦ ለሀያ ቀናት አገልግላ ብትመለስም፣ ከዚህ በላይም በሙያዋ በተመሳሳይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት እንደምትፈልግ ገልፃለች።