ትናንሾቹ የጦርነት ሰለባዎች

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል በተነሳው ጦርነት ምክንያት ወደ ሱዳን ከተሰደዱ መሃከል ነፍሰጡሮች እና አራሶች ሲኖሩ ባዛው በሱዳን ካምፕ ውስጥም ልጆቻቸውን የተገላገሉ እናቶች አሉ፡፡ የካምፑ አስተዳዳሪዎች ስደተኞቹን ወደ ሌላ ጣቢያ የማዘዋወር ዕቅድ ቢኖራቸውም እናቶቹ ግን፤ ገና ከተወለዱ የቀናት እድሜ ያላቸውን ሕጻናት ይዞ ወደሌላ ካምፕ መሄዱ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጿ ሄዘር ሙርዶክ ከሱዳን ሃምዳይት የላከችውን ዘገባ ኤደን ገረመው እንደሚከተለው አጠናቅራዋለች፡፡