አንጋፋው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መስራች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የአደባባይ ምሑር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በ90 ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፏል። ዛሬ የተቋቋመው ከቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ ለክብራቸው በሚመጥን መልኩ በሚሰናደ ሥነ ሥርዓት ሽኝታቸው ይከናወናል ብሏል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ፕሮፌሰርን መስፍንን በቤት ውስጥ የምታግዛቸው ልጅ በኮቪድ- 19 መያዟ ከታወቀ በኋላ እርሳቸውም ምርመራ ሲደረግላቸው በቫይረሱ መያዛቸው ስለተረጋገጠ ወደቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ሆስፒታል ተወስደው የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ነበር።
በኋላም ላይ በዚያው ሆስፒታል ለዐሥራ አንድ ቀናት የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ማክሰኞ መስከረም 19/2013 ዓ.ም ምሽት አምስት ሰዓት አካባቢ ሕይወታቸው አልፏል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ለክብራቸውበሚመጥን መልኩ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውን ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ያሬድገልፀዋል።
(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5