አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አረጋገጠ

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ማምሻውን ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን በቦታው የሚገኙ ምንጮችለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። የአርቲስቱ ሕይወት ማለፍ ከተሰማ በኋላ “ለቡስታር” በተሰኘ ሆስፒታል ተገኝተው ሕይወቱማለፉን ያረጋገጡት ምንጮች አርቲስት ሃጫሉ በጥይት የተመታው ከምሽቱ 3፡30 ገደማ ገላን እየተባለ በሚጠራውኮንደሚኒየም አካባቢ እንደሆነ ገልፀዋል።

ማምሻውን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው መረጃውለፖሊስ ከደረሰ ጀምሮ ክትትል ሲደረግ እንደነበር ገልፀው፤ እስካሁን የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንተናግረዋል።በድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉትን ሰዎች ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

(ተጨማሪ መረጃዎችን ከፖሊስ ለማጣራት ሙከራ እያደረግን ነው እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን።)