“የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከያና መቆጣጠሪያ ረቂቅ ዐዋጅ” ፤ ተጨማሪ ውይይት ሳይደረግበትና ሳይከለስ ባለበት ሁኔታ ከፀደቀ ሐሳብን የመግለጽ ነፃነትን ይጋፋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የረቂቅ ዐዋጁ አቀራረፅና የቋንቋ አጠቃቀሙ ለትርጉም ክፍት የሆኑ ዓረፍተ ነገሮች በማካተቱ ሐሳብን በመግለፅ ነፃነት ላይ ገደብ ሊጥል ይችላል በማለት በአገር ውስጥ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም ስጋታቸውን አጋርተዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ዐዋጁ ዜጎችን ከጥቃት ለመታደግ ታሳቢ ተደርጎ የተረቀቀና አስፈላጊ ነው ብሏል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5