“በአፍሪካ አሕጉር ሰላም እንዲሰፍን በመፈለግና ከኤርትራም ጋር የነበረው ግጭት እንዲያከትም በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የያዙት ቆራጥነት፣ ደፋርነት፣ ጥንካሬና የአመራር ብቃትን ያሳያል” ብሏል የውጭ ጉዳት ሚኒስቴር ማይክ ፓምፔዮ መልዕክት።
“ይህንን ከፍ ያለ ጊዜም ከኢትዮጵያና ከአሕጉሪቱ ሕዝብ ጋር አብረን እናከብራለን” ያሉት ማይክ ፓምፔዮ አያይዘው፤ “ዛሬ የተሻለ ብልፅግናና የሰላማዊ መፃዒ ዘመንን ተስፋ የተሞሉ አፍሪካውያያን አዲስ ትውልድ ያሉበት ጊዜ ነው” ብለዋል። በመቀጠልም አፍሪካ ውስጥ ዴሞክራሲና ሰላምን ለማጠናከር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የያዙት ጥረት መጪ የዓለም መሪዎች በየአካባቢያቸ የገንቢ ለውጥ ምክኒያት እንዲሆኑ ያነቃቃቸዋል - ብለዋል። “የኖቤል ሽልማት ሰጪ ኮሚቴም ዶ/ር አብይ ሰላም እንዲጎለብትና በዓለማችን ግጭቶች እንዲያበቁ ላደረጓቸው የላቁ ጥረቶች እውቅና በመስጠቱ አድናቆታችንን እንገልፃለን” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕምድ ያስተላለፉትን የደስታ መግለጫ መዕክት ቋጭተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የዩይትድ ስቴትስ ልማት ኤጀንሲ (ዩ. ኤስ. ኤ. አይዲ) አስተዳደር ማርክ ግሪንም ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደስታቸውን ገልፀዋል። አያይዘውም “ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሰላምና ዓለም አቀፍ ትብብርን እንዲያጠናክሩ የሚያደርጓቸውን ጥረቶች በተለይ ደግሞ ከጎረቤት ኤርትራ ጋር የነበረውን የድንበር ግጭት እንዲፈታ የወሰዱትን ቆራጥ ተነሳሽነት የሚያጎላ ነው” ብለዋል።
“ይህንን የተከበረ ሽልማት በማግኘታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር አብረን እንደሰታለን።” ብለዋል።
ማርክ ግሪን በመልዕክታቸው ማጠቃለያም፤ “ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲና የምጣኔ ኃብት ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግና በአካባቢውም የነቃ ሚና ለመጫወት ለያዙት ተግባር ዩናይትድ ስቴትስ ሙሉ ድጋፍ መስጠቷን በፅናት ትቀጥላለች።” ብለዋል።