"ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ዕድገት የተቃዋሚዎች ብሶት መደመጥ አለበት"ተንታኞች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የኦሮምያ ክልል ሲካሄድ በቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ድርጊቱ የሀገሪቱን የምጣኔ ሃብት ዕድገት ሊያሰናክል ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።ተንታኞች ግን የምጣኔ ሃብት ዕድገቱ እንዲቀጥል አንዱ ቁልፍ ርምጃ የተቃዋሚዎችን ብሶት አድምጦ መፍትሄ መስጠት መሆኑን ይመክራሉ።