"አሜሪካውያኑ ወላጆች ለኢትዮጵያዊ ልጆቻቸው ማንነታቸውን የሚያስተምርላቸው ሰው ይፈልጋሉ"
Your browser doesn’t support HTML5
ተፈራ ሃይሉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማደጎ የሚመጡትን ህፃናትና ወጣቶች ከኢትዮጵያነታቸው ጋር የመተዋወቂያ መድረክ ይሆን ዘንድ ኔትዎርክ ኦፍ ፋሚሊ ሰርቪስ ፕሮፌሽናልስ የተሰኘ ገባሬ ሰናይ ድርጅት አቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ድርጅቱ በአሜሪካን ሃገር ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የማደጎ ልጆች የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል በማስተማር ላይ ይገኛል። የማህበራዊ ሚድያ ፌስቡክ በመክፈት ልጆቹ እርስ በእርስ ችግሮቻቸውን እንዲመካከሩና እንዲፈቱ የመወያያ መድረክ ከፍቷል።