አፍሪቃ በጋዜጦች

A man reads a newspaper with headlines reading 'Gov't Takes More Measures Against Ebola, as fear about the virus spread in the city of Monrovia, Liberia, July 31, 2014.

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። በኢትዮጵያ ሲጃራ ማጨስ እየቀረ መሆኑ ተገለጸ፣ ጃፓን ለአፍሪቃ እድገት አንድ ትሪልዮን የን ለመስጣት ማቀድዋ ታወቀ፣ የቻይና የገንዘብ ዋጋ መውረድ በአፍሪቃ ላይ የሚኖረው ተፅእኖ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ፕሮግራማችን የምንመለከተው።

የኢትዮጵያ ቡና ቤቶችና ባሮች ከስጃራ ንጹህ እየሆኑ መሆናቸውን Mail and Guardian የተባለው ድረ ገጽ ሲዘገብ መቐለ ከተማን እንደምሳሌ ይጠቅሳል። በመቐለ ከተማ ባሮችና ቡና ቤቶች ሞቅ ያሉና በሰዎች የተሞሉ ናቸው። ሆኖም እንደድሮው በሲጃራ ጭስ የታፈኑ አይደሉም ይላል ዘገባው።

የአፍሪቃ የካንሰር ማህበር ባደረገው ጥናት መሰረት እአአ ከ 1990 እስከ 2010 አም ባለው ጊዜ በአፍሪቃ ከደቡብ አፍሪቃ በስተቀር በ 70 ከመቶ ከፍ ብሏል። እስከ 2030 አም ባለው ጊዜ(በ 10 አመታት ውስጥ ማለት ነው) ሲጃራ የሚያጨሱ አፍሪቃውያን ብዛት በአርባ ከመቶ ሊጨምር እንደሚችል ጥናቱ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ሲጋራ ማጨስን በማገድ ረገድ የመጀመርያዋ የአፍሪቃ ሀገር ባትሆንም እስካሁን ባለው ጊዜ ለማስከበር ከሚሞክሩት ጥቂት ሀገሮች አንዷ ናት። የኬንያ መዲና ናይሮቢ ማጨስ የሚቻልባቸው ቦታዎችን ለይታለች። መንገድ ላይ ማጨስም ክልክል ነው። ሆኖም ህጉ በሰፊው ይጣሳል ይላል Mail Guardian ላይ የወጣው ዘገባ።

--------

የጃፓን ታይምስ ጋዜጣ ድረ-ገጽ በበኩሉ የመንግስትን ምንጭ ጠቅሶ በዘገበው መሰረት ጃፓን ከመጪው አመት አንስቶ በሶስት አመታትት ውስጥ አንድ ትሪልዮን የን የሚሆን ገንዘብ ለአፍሪቃ እድገት የመስጠት አላማ አላት።

የጃፓን መንግስት ስለ ገንዘቡ እርዳታ የሚያስታውቀው በመጪው አመት ኬንያ እንዲደረግ በታቀደው የጃፓንና የአፍሪቃ አለም አቀፍ ጉባኤ እንደሆነ ድረ-ገጹ አውስቷል። በተፈጥሮ ሀብት በበለጸገችው አፍሪቃ የቻይና ተጽእኖ እየበረታ በሚሄድበት በሁኑ ወቅት ጃፓን ለአፍሪቃ የምታደርገው እርዳታ እየጨመረ መሄዱን የምትሰጠው እርዳታም ከመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ወደ እርሻና ምግብ ዘርፋ እየለወጠች መሆንዋን ድረ-ገጹ ጠቅሷል። ሌላ ርእስም አለን። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ;

Your browser doesn’t support HTML5

Africa Press Review 8-21-15