Brookings የተባለው ዋሽንግተን ሲዲ የሚገኘው የጥናትና ምርምር ተቋም የሚያወጣው ድረ-ገጽ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ አፍሪቃን በጎበኙበት ወቅት ፕረዚዳንታዊ ስልጣን ገደብ እንዲኖረው ያደረጉትን ንግግር መሰረት በማድረግ ባቀረበው ድሁፍ እአአ በ 1990 ዎቹ አመታት በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ከተወዳዳሪ አልባ ተወዳዳሪዎች ወደ ሚኖርዋቸው ምርጫዎች እንደተሸጋገሩ ይገልጻል።
አፍሪቃ ውስጥ እአአ በ 1980 ዎቹ አመታት ተወዳዳሪዎች የቀረቡባቸው ምርጫዎች የተካሄዱባቸው የአፍሪቃ ሃገሮች ከሀያ በታች ነብሩ። በ 1990 ዎቹ አመታት ግን ወደ 72 ከፍ ማለታችውን ጽረ-ገጹ ጠቁሟል። ከዛ ጋር ተያይዞም ሀገሮች መሪዎች በስልጣን ላይ የሚቆዩበትን የጊዜ ገደብ አስቀመጡ። የስልጣን ጊዜውም ከሰባት ወደ አምስት ወይም ከዛ ወዳነሰ ተቀነሰ። አዳዲስ ሀግ-መንግስቶችም ወጡ ይላል ጽሁፉ።
ይሁንና ተወዳዳሪ የሌላቸው ምርጫዎችና መፈንቅለ መንግስታት እየቀነሱ ቢሄዱም በውድድር የተካሄዱ ምርጫዎች ወደ አመራር ሽግግር የሚያመሩት ብዙም አልተበራከቱም። ይህም ወደ ኋላ የመመለስ ስጋት እያሳደረ ነው። ግልጽ በሆነ ውድድር ስልጣን ላይ የወጡ መሪዎች ሳይቀሩ በስልጣን የጊዜ ገደብ አስፈላጊነት ላይ የጥያቄ ምልክት እያስቀመጡ ነው። በአህጉሪቱ ዙርያ ህገ መንግስቶችን ለመለወጥ ሃሳቦችን የሚያቀርቡ ፐረዚዳንቶች ብዛት እየተበርከተ ነው። ይህም መረጋጋትን ሳይሆን ወደ ኋላ መቅረትን ያስከትላል ሲል ብሩኪንግስ ጽረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ያወሳል።
--------
The Globe and Mail የተባለው የካናዳ ጋዜጣ ድረ-ገጽ በበኩሉ ኦባማ አፍሪቃን እያጡ መሆናቸውን የሚግልጽ ዘገባ አውጥቷል። ፕረዚዳንት ኦባማ በቅርቡ በአፍሪቃ ያካሄዱት ጉብኝት በንግግርና በተምሳሌት ደረጃ መልካም ነበር። ነገር ግን የአፍሪቃ መሪዎች በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ማክበር ረገድ ያላቸውን ድክመት በይፋ የገሰጹ ቢሆንም ጉብኝታቸው ለአፍሪቃ ያቀረበው ተጫባጭ ነገር የለም ይላል።
ይህን ጽሁፍ ያቀረቡት በ United States የካናዳ አምባሳደር የነበሩት Derek Berneyና በካርልተን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት Fen Osler Hampton ናቸው።
አፍሪቃ የማያባሩ የድህነት፣ የሙስናና የጸጥታ ችግሮች ቢፈራረቁባትም ተጨባጭ የሆነ ብሩህ ተስፋ እየታየባት ነው። United Statesና ሌሎች በርካታ የምዕራብ ሀገሮች ግን ሁኔታውን እየተጠቀሙበት አይደለም ሲል ድረ-ገጹ ያትታል።
አዎንታዊ የሆነ ህዝባዊ ዝንባሌ የአፍሪቃን የኢኮኖሚ ትንሳኤ እያንቀሳቀሰ ነው። ኢትዮጵያን፣ አንጎላን፣ ቦትስዋናንና ታንዜንያን በመሳሰሉት ሃገሮች ከፍተኛ የኢኮኖሚ እደገት እየታየ ነው። ይሁንና ምዕራቡ አለም ቻይና ለአፍሪቃ በምትሰጠው ትኩረትና በምታከናውናቸው ተጭባጭ ተግባሮች እየተበለጠ ነው። ቻይና ከሰሃራ በመለስ ባሉት የአፊርቃ ሀገሮች የምታፈሰው መዋዕለ-ነዋይ ከሶስት አመታት በፊት $18.55 ቢልዮን ዶላር ደርሶ ነብር የሚሉት ዘገባዎች በዛሬው ዝግጅታችን ተካተዋል። የአፍሪቃ ሚልዮነሮች ዘገባም አለን። ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5