Your browser doesn’t support HTML5
ጆን ኬሪ ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የፋርስ ባሀርሰላጤ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ የዩናትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት በኢራንና በአሜሪካ በተመራው የስድስት ሃገሮች ቡድን መካከል የተደረገውን ስምምነት ባያጸድቅ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭትና ጦርነት እንዲባባስ የሚያደርግ መሆኑን እንደሚረዱ እተማመናለሁ ብልዋል።
“ይህን ስምምነት ባናደርግ ኑሮ የኢራኑ አያቶላ እነዚህ ሰዎች ያስገኙት ነገር ስለሌለ ከነሱ ጋር የምንደራደርበት ምክንያት የለም ባሉ ነበር። የስራ ባልደረቦቻችን በኢራን ላይ ማዕቅቦች የተጣሉት ወደ ድርድርና ስምምነት እንድታመራ ለማድረግ ነው እያሉ ማዕቀቡ እንዲቀጥል የሚደግፉበት ምክንያት ምንድነው? አሁን የተገኘውን ስምምነት ባይቀባሉ በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ትልቅ አደጋ ይደቀናል” በማለት ጆን ኬሪ አስገንዝበዋል።
የዩናትድ ስቴስ አስተዳደር ኢራን የታሰሩት አሜሪካውያን እንዲፈቱ መጠየቅን የተካተቱባቸው አጀንዳዎችን ጨምሮ መግፋት ነበረበት የሚሉ ነቀፊታዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል። ጆን ኬሪ ታድያ ሌሎች ነጥቦችንም ጨምረን ቢሆን ኖሮ የትም አንደርስም ነበር ብለዋል።
“ከዚህ በፊትም እንደገለጽነው በኢራንና በአለም ማህበረሰቡ ወይም በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በሚደረገው ድርድር ሌሎች ነጥቦችንም አክለን ቢሆን ኖሮ ለ 10 አመታት ያህል ብንደራደርም እንኳን የትም አንደርስም ነበር። ነጥቡ የኑክሌር ጉዳይ በመሆኑ ከተደረሰው መሻሻል አንጻርም ሲታይ ሌሎች ጉዳዮችን ለማንሳት የሚይስስችለን ጊዜ አልነበረንም”ብለዋል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።