Your browser doesn’t support HTML5
የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የርእስ-አንቀድ ቦርድ ያወጣው ጽሁፍ የፕረዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት የተሳሳተ መልእክት ያስተላልፋል ይላል።
ፕረዚዳንት ኦባማ ከስድስት አመታት በፊት ለጋና ምክር ቤት ንግግር ባደረጉበት ወቅት “ለአፍሪቃ የሚያስፈልጓት ጉልበተኞች ሳይሆኑ ተቋማት ናቸው" ብለው ነበር። ከሁሉም በፊት ጠንካራና ዛላቂ ዲሞክራስያዊ መንግስታትን መደግፍ አለብን ሲሉም ለአፍሪቃ መሪዎች ጥሪ አቅረበው ነበር። ነገር ግን ፕረዚዳንቱ ይህን ንግግራቸውን የረሱ ይመስላል ይላል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ድር-ገጽ ላይ የወጣው የርእሰ-አንጽ ቦርድ አመለካከት።
ታሪካዊ የሆነ ሰላማዊና ዲሞክራስያዊ የመንግስት ለውጥ ያደረገችውን ናይጀርያ ሳይጎበኙ ሰብአዊ መብት ወደ ማታከብረው ኢትዮጵያ ለመሄድ መወሰናቸው ለማመን ያዳግታል ይላል ዋሽንግተን ፖስት ድረ-ገጽ ያወጣው አቋም።
በሌላ በኩል ግን ቫንጋርድ የተባለው የናይጀርያ ጋዜጣ ድረ-ገጽ በዘገበው መሰረት ፕረዚዳንት ኦባማ የናይጀርያውን ፕረዚዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪን በመጪው ወር በዋይት ሃውስ ቤተመንግስት ተቀብለው ያነጋግራሉ። ፕረዚዳንት ኦባማ የናይጀርያውን ፕረዚዳንት የሚያስተናግዱት በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ለተካሄደው ዲሞክራስያዊ ፕረዚዳንታዊ ምርጫ የአንድነት ስሜት ለመግለጽ እንደሆነ ቫንጋርድ ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቁሟል።
በሩስያ የኢትዮጵያ አማባሳደ ግሩም አባይ ደግሞ የኢትዮጵያና የሩስያ ግኝኑነት ከርዕዮተ-አላማዊ አመለካከትና ከሁኔታዎች መለዋወጥ ጋር የተለያዩ ገጽታዎች የተንጸባረቁበት ቢሆንም ከሩስያ ጋር እአአ በ 1898 አም ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት የመሰረተችው ኢትዮጵያ ሩስያን ምን ጊዜም ቢሆን በአዎንታዊ መልክ ታያለች ሲሉ አምባሳደር ግሩም መናገራቸውን የሞስኮ ታይምስ ድረ-ገ ዘግቧል።
እአአ በ 1895 እና 96 አም ኢትዮጵያ ከኢጣልያ ጋር ትዋጋ በነብረበት ጊዜ ሩስያ ለቆሰሉት ኢትዮጵያውያን የህክምና እርዳታ ታደርግ እንደነበር፣ የሩስያ ቀይ መስቀል በአዲስ አበባ የከፈተው የደጃች ባልቻ መታሰብያ ሆስፖታል አሁንም እንዳለ፣ በሶቭያት ህብረት ዘመን ብዙ ተማሪዎች የትምህርት እድል ያገኙ እንድነበር፣ በአሁኑ ወቅት ግን በሞስኮ የወዳጅነት ዩኒቨሲቲ የሚማሩት ኢትዮጵያውን ስምንት ብቻ እንደሆኑ በአሁኑ ወቅት በሩስያ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ሩስያውያን 163 ብቻ መሆናቸውን አምባሳደር ግሩም ማስገንዘባቸውን ሞስኮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቁሟል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።