የትላንቱን ያስተናጋጅ ኢኳቶሪያል ጊኒና ጋና የግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያ ”የጦርነት ቀጠና ይመስል ነበር ሲል ነው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን የገለጸው። በረብሻው ምክንያት ጠዋታው ለጊዜው ተቋርጦ ነበር፥ ተጫዋቾችና ጎብኚ ደጋፊዎች ላይ ውርወራ ተካሂዷል።
መጫወቻ ሜዳው ላይ ከተወረወሩ ቁሳቁሶች መካከል የመስታወት ስባሪ፥ ድንጋይና የስታዲየም መቀመጫ ተገኝቷል። አስተናጋጇ በፀጥታ ጥበቃ መላላት በድጋሚ ተወቅሳለች። ድርጊቱ አሳፋሪና አሳዛኝ በመሆኑ እንደማይደገም ተስፋ ተደርጓል።
ውድድሮቹን በተመለከተ፥ በመርሃ ግብሩ መሠረት ነገ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከኮንጎ ዲሞክሪክ ሪፐብሊክ ለደረጃ፥ ዕሁድ ጋና ከአይቮሪኮስት ለዋንጫ ይጫወታሉ።
Your browser doesn’t support HTML5