ኢትዮጵያና ጂቡቲ የኢኮኖሚ ውህደት ለመፍጠር እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል። ውሎ አድሮም ወደ ፖለቲካዊ ውህደት የማምራት እድል እንዳለው ይገመታል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያና ጂቡቲ የኢኮኖሚ ውህደት ለመፍጠር እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል። ውሎ አድሮም ወደ ፖለቲካዊ ውህደት የማምራት እድል እንዳለው ይገመታል።
የጅቡቲ ፕረዚዳንት ኢስማዔል ዑመር ጊሌ ራሳቸው የኢትዮጵያና የጂቡቲ ግንኙነት ጽኑ መሰረት እየጣለ በመሄዱ የሁለቱ ሀገሮች ህዝቦች ፍላጎት ከሆነ ቢዋህወዱ መልካም ነው ሲሉ እንደተናገሩ ተዘግቧል።
ይህን መሰረት በማድረግም ስለጉዳዩ ሲጽፉ የቆዩት ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያ እንዲያብራሩልን ጋብዘናል። ዶክተር ገላውዲዮስ በሲቲ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ ኒው ዮርክ ሌማን ኮሌጅ የአፍሪቃና የአፍሪቃን አሜሪካን ጥናቶች አስተማሪ ናቸው።
ዶክተር ገላውዲዮስን ያነጋገረችው አዳነች ፍሰሀየ ናት። ዶክተር ገላውዲዮስ ከምጣኔ-ሀብታዊ ውህደት ወደ ፖለቲካዊ ውህደት መሸጋገር አለባቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ ይጀምራሉ። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5