አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። አንድ ስደስተኛውን የኢትዮጵያ መሬት የማልማት እቅድ ወጣና ብሪትናያ ለኢትዮጵያ ፖሊስ ከምትሰጠው እርዳታ ቀነሰች የሚሉ ይገኙባቸዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ በ16 አመታት ውስጥ ከሀገሪቱ መሬት አንድ ስድስተኛ የሚሆነውን ለማልማትና በአዲስ መልክ ዛፎችና አዝርእት ተተክለው አረንጓዴ እንዲሆኑ ለማደረግ እንዳቀደች theguardian ድረ-ገጽ ዘግቧል።
ድረ-ገጹ ቀጥሎም ከ 15 አመታት በፊት ትግራይ ውስጥ አብረሀ-ወአጽበሀ አከባቢ ያሉት መንደሮች አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሰው ስለነበር ሰው አልባ ሊሆኑ ተቃርበው እንደነበር ይገልጻል። ኮረብታዎቹ ተራቁተው ህብረተሰቡም አንዴ ድርቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጎርፍ ይፈራረቅበት ነበር። መሬቱ እየተሸረሸረና እየተጠራረገ በመሄድ ባዶ ቀርቶ ነበር። ህዝቡም የምግብ እርዳታ ጥገኛ ለመሆን ተገዶ ነበር። አሁን ግን የአብረሀ ወአጽበሀ አከባቢ ፈጽሞ ተለውጧል። ሊከተል የነበረው መቅሰፍትም ተወግዷል ይላል ጋርዲያን ድረ-ገጽ።
ትግራይ ውስጥ የተራቆቱ መሬቶችን ለማልማትና መልሶ ለማቋቋም የተደረገው ጥረት ስፋት ሲታይ በአለም ደረጃ ተወዳዳሪ የለውም። የትግራይ ህዝብ ከቀርብ አመታት ወዲህ የተራቆተውን መሬት ለማስተካከል የቆፈረው መሬትና ያደቀቀው አለት ግብጻውያን ፒራሚዶችን ለመገንባት ሲሉ በብዙ ሺህ አመታተ ውስጥ ካደረጉት የበለጠ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ Chris Reij መናገራቸውን ጋርዲያን ላይ የወጣው ዘገባ ጠቅሷል። ሙሉዉን ዘገባ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5